mother

ሩትም። ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤

መጽሐፈ ሩት 1 : 16

ሰለዚህ ሕፃን ጸለይሁ፤

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1 : 27

ደኅነኛውም የነበራት ሴት አንጀትዋ ስለ ልጅዋ ናፍቆአልና። ጌታዬ ሆይ፥ ደኀነኛውን ለእርስዋ ስጣት እንጂ አትግደል ብላ ለንጉሡ ተናገረች። ያችኛይቱ ግን። ይከፈል እንጂ ለእኔም ለአንቺም አይሁን አለች።

መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ። 3 : 26

መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ።

መዝሙረ ዳዊት 113 : 9

እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።

መዝሙረ ዳዊት 127 : 3

መዝሙረ ዳዊት 31 : 25

አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።

መዝሙረ ዳዊት 143 : 8

እግዚአሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።

መዝሙረ ዳዊት 46 : 5

የዳዊት መዝሙር። እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።

መዝሙረ ዳዊት 23 : 1

እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።

መዝሙረ ዳዊት 28 : 7