hope
አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።
መዝሙረ ዳዊት 71 : 5
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።
መዝሙረ ዳዊት 39 : 7
እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፥ በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ።
መዝሙረ ዳዊት 71 : 14
አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ፤ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
መዝሙረ ዳዊት 25 : 2
አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።
መዝሙረ ዳዊት 25 : 21
ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ።
መዝሙረ ዳዊት 62 : 10
ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።
መዝሙረ ዳዊት 65 : 5
አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን።
መዝሙረ ዳዊት 33 : 22
ማለዳ ጮኽሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።
መዝሙረ ዳዊት 119 : 147
አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፥ በቅዱሳንህም ዘንድ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ።
መዝሙረ ዳዊት 52 : 9

